"እንኳን ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ" በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ

በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ የ128ኛውን የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የአንድነት ጥሪና የአገልግሎት ተደራሽነትን ለዜጎች አስፍቶ የማዳረስ ዝግጅነቱን ገለጠ።

Ambassador Hadera Abera Admasu I.jpg

Hadera Abera Admasu, Ethiopian Ambassador to Australia. Credit: Supplied

ኤምባሲው በአውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድና በአካባቢው አገሮች ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈው የድል በኣል መልዕክቱ፤

"የዛሬ 128 ዓመት አገራችን የተጋረጠባትን ወረራ ለመቀልበስ ጀኞች አባቶቻችንና እናቶቻችን ከሁሉም የአገራችን ክፍሎች በአንድነት በመዝመት አጥንታቸውን ከስክሰውና ደማቸውን አፍሠው ጠብቀው እንዳቆዩን ሁሉ አገራችንን አንድነቷና ሰላሟ ተጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅብን፤ ለዚህም የሁሉም ዜጎችና የኢትዮጵያ ተወላጆች ትብብር እንደሚጠበቅ ያምናል" ብሏል።

አክሎም "በቀጣናው አገራት ነዋሪ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶችን በሰከነ መልኩ በሰላማዊ መንገድ፣ በንግግርና በድርድር ለመፍታት ለሚደረጉ አገራዊ ትረቶች መሳካት የሚጠበቅባችሁን አስተዋፅዖ እንድታበረክቱ አገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን" ሲል አሳስቧል።

በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ "ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማስፋትና አገልግሎቱንም ዜጎች በሚኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ ተደራሽ ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር በቅርበት ለምሥራት ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ እያረጋገጥን ለምትሰጡን አስተያየትና ድጋፍ ሁሉ እናመሰግናለን" በማለት መሰናዶውን አመላክቷል።

Share
Published 2 March 2024 7:18pm
Source: SBS

Share this with family and friends