በድመቶች እና አይጦች መካከል ሊደርግ የታሰበ ሰርግ- ታሪኩ የተወሰደው ከአማርኛ ቋንቋ ነው ::

EPISODE_WEDDING CATS.jpg

‘The Wedding of Cats and Rats’ - a story from the Amharinya language Credit: Grace Lee

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

የድርቁ ወቅት በጣም ባየለበት ወቅት ፤ በመርሀቤቴ ከተማ የሚኖሩ እውቅ ድመቶች ድንቅ የሚባል ሀሳብን ይዘው ብቅ አሉ ፤ ይሁንና የእድሜ ልክ ባላንጣዎቻቸው እና ብልሆቹ አይጦችም እንዲሁ የራሳቸውን ሀሳብ ይዘው ብቅ አሉ ፤


የዚህ ሳምንት ታሪክ የተገኘው በምስራቅ አፍሪካ ከሚነገሩት ቋንቋዎች አንዱ ከሆነው አማርኛ ቋንቋ ነው ። ታሪኩ ድንቅ ልብ አንጠልጣይ በሆኑ ገጸ- ባህሪያት የተገነነባ ሲሆን ፤ አንዳንዶቹም በቤትዎ ውስጥ ሊያውቋቸው የሚችሏቸውንም ጭምር አካቷል ።

ተራኪ እና አቅራቢ ፤ አሊስ ኩዊን - የታሪኩ አማካሪ እና ተርጓሚ ማርታ ጸጋው - አርታኢ ፡ ማርስል ዶርኒ - ድምጽ ማርታ ጸጋው ፤ ጌታሁን ሰለሞን ፤አላ አል-ተሚሚ ፤ ሃና ያሲን ፤ የድምጽ ቀርጻ ኢንጂነር ፤ ቭላድ ላድማን ፤ ዋና አቀናባሪ እና የድምጽ ዲዛይን እና ሙዚቃ ፤ ኪረን ሩፍሊስ ።

ከስቶሪ ግሎብ ተጨማሪ ተከታታይ ታሪኮችን ካሻዎ ፤ ከአፕል ፖድካስት ፤ ጉግል ፖድካስት ፤ ስፖቲፋይን ወይም ኤስ ቢ ኤስ ራድዮ አፕን ይከታተሉ።


በድመቶች እና አይጦች መካከል ሊደርግ የታሰብ ሰርግ

 
ተረት ተረት - የላም በረት

ታሪኩ የሰርግ ታሪክ ነው

ትልቅ ድግስ ተደርጎ ብዙዎች በአንድ ላይ የሚዳሩበት ሰርግ ነው።

በድመቶች እና አይጦች መካከል የሚደረግ ሰርግ ።

ይህ ታሪክ የተከናወነውም አነስተኛ በሆነችው እና መርሀቤቲ በመባል በምትታወቀው ከተማ ነው። በዚያን ዘመን የከተማዋ አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች የሚተዳደሩት በግብርና ሙያ ሲሆን ፤ ጤፍ ፤ በቆሎ ፤ ሸንኮራ እና ማሽላን በዋነኛነት የሚያመርቱ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ አትክልት እና ፍራፍሬዎችንም ያመርታሉ። እንደ አብዛኛዎቹ ከተሞችም የበጋው ወራት በጣም የሚሞቅ ሲሆን ክረምቱም እንዲሁ ቀዝቃዛ ነው።የአካባቢው ገበሬዎች እንደ ሌሎቹ ሁሉ እርሻቸው በዝናብ ላይ የተመሰርተ ነው።

ዝናብ ካልዘነበ ፤ ሁሉም ይቸገራሉ ። ወንዞቻቸው ይደርቃሉ ፤ ገበሬዎች ፤ ከብቶቻቸው እና ሌሎች እንስሳት እንደ ድመት እና አይጥ ያሉ ሳይቀሩ በረሀብ ይሰቃያሉ። ድመቶችን እና አይጦችን ስታውቋቸው ሁለቱም እንስሳት የሚያስቡት ራሳቸውን ብልጥ አድርገው ነው ። አይጦች በበኩላቸው በመጠናቸው ትናንሽ ፤በቁጥራቸው ብዙ እና በፍጥነት ለመሰወር የሚችሉ ናቸው ተብሎ ስለሚታመን ፤ እነሱን በቀላሉ አታልሎ በፍጥነት ይይዛሉ የሚባሉት ደመቶች ናቸው ።

በዚህም መሰርት በመርሀቤቴ የሚኖሩት ሁሉም ገበሬዎች ሰብላቸውን ከአይጦች ጥቃት ለመከላከል ድመቶች አሏቸው። ምንም እንኳ የድመቶች ምርጥ ምግብ ሳምባ ቢሆንም ገበሬዎች ቁርጥራጭ ስጋዎችንም በመመገብ ይንከባከቧቸዋል ። አንዳንድ ጊዜ በጋው በጣም ጸሀያማ ይሆናል።በሌላ ጊዜ ደግሞ ክረምቱ አነስተኛ ዝናብን ብቻ ይሰጣል።

ነገር ን በዚያ አመት በክረምትም ሆነ በበጋው ፤ በድፍን መርሀቤቴ ምንም ዝናብ ሳይጥል ቀረ። ስለሆነም ምግብን ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ሆነ ። ገበሬዎችም መተኪያ ላይኖር ይችላል በሚል ስጋት ፤ እንደ ሌላው ጊዜ ከብቶቻቸውን ማረድ አቆሙ ። እውነታው ደግሞ ድመቶች ከሌሎች እንስሳቶች በበለጠ ስጋን ይፈልጋሉ ። ስለሆነም ለእነሱ የሚሆን ምግብ ማግኘት ከባድ ሆነ ፤ ሲታዩም እድገታቸውም የቀጨጨ እና የተዳከሙ ሆኑ ።

ከድመቶቹም መካከል አቶ ማንደፍሮ የሚባሉ ነበሩ ።

ማንደፍሮ ማለት ፤ ማን ይደርስበታል ፤ ማን ያሸንፈዋል ማለት ነው ። ድመቶቹም አቶ ማንደፍሮን መሪያችን ብለ የሚጠሩ ሲሆን እሳቸው እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሁዳድ በዚያ መንደር ሲኖሩ በርካታ ወቅቶች ሲመጡ እና ሲሄዱ ሲፈራረቁ አይተዋል። ወ/ሮ ሁዳድ እና ባለቤታቸው አንድ ምሽት በባህሩ ዳርቻ እየተጓዙ ፤ ወ/ ሮ ሁዳድ በህይወት ዘመኔ ካየሁት ድርቅ ሁሉ ይህ እጅግ የከፋ ነው ሲሉ ላባለቤታቸው ተናገሩ ።

የወይዘሮ ሁዳድ ስም የተወሰደውም በአቅራቢያቸ ካለ ወንዝ ሁዳድ ውሀ ወንዝ ሲሆን ትርጓሜውም የውሀ ምንጭ ማለት ነው። ወ/ሮ ሁዳድ የመንደራቸው ውሀ ጎድሎ ሲያዩት በቁጭት ተብሰከሰኩ። ውዴ አንድ እቅድ እያሰብኩ ነው አሉ አቶ ማንደፍሮ ለባለቤታቸው።

ነገር ግን እቅዳችን በተግባር እንዲውል ፤ ከዚህ በኋላ እኛ ለአይጦች ባላንጣ እንዳልሆንን እና በመካከላቸን ያለው ጠላትነት እንደሚያበቃ አድርገን አይጦችን ማሳመን አለብን ።

ወ/ሮ ሁዳድም ባለቤታቸው ንግግራቸውን እስኪጨርሱ በጥሞና ካዳመጡ በኋላ ማሰላሰላቸውን ቀጠሉ ። እኔ በጣም እወድሀለሁ እንዲሁም እተማመንብሀልሁ ነገር ግን እቅዱ በጣም አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ፍርሀታቸውን ገልጸው ሀሳቡን ግን ለማህበረሰባችን አባላት ማቅረብ ይኖርብናል አሉ ።

በሚቀጥለው ቀን አቶ ማንደፍሮ በጠሩት ስብሰባ ተገኝተው ፤ በመንደራቸው ከሚገኘው ትልቁ የጥድ ዛፍ ስር ከፍ ብሎ በሚታየው ጥቁር ድንጋይ ላይ ተቀመጡ ።

በዚሪያቸውም ባለቤታቸው እና ስድስት ልጆቻቸው እንዲሁም ፤ የመርሀቤቴ ከተማ ነዋሪ ድመቶች በሙሉ ተሰበሰቡ። እያንዳንዳቸውም መሪያቸው ይህንን አስቸኳይ ስብሰባ ለምን እንደጠሩ ለማወቅ ጉጉታቸው በጣም ጨምሯል ።

ድመቶቹ የሚያሰሙትን የሚያውታ ድምጽ እንዳቆሙ (ድመቶችን የምታውቁ ከሆን ለማቆም ጊዜን ይወስዳሉ )

አቶ ማንደፍሮ ንግግራቸውን ጀመሩ ።

እንደምታቁት ፤ ሲሉ ጀመሩ ፤ የምግብ እጥረት አጋጥሞናል ፤ አሰሪዎቻችን ማለትም የሰው ልጆች ለዚህ ምንም መፍትሄ የላቸውም ።እኔ ለዚህ መፍትሄ አለኝ ፤ ነገር ግን ከዚያ በፊት የእናንተን ሀሳብ መስማት እፈልጋለሁ አሉ ።

ከጥቁሩ ድንጋይ በስተቀኝ የተቀመጡ አንድ አዛውን ድመት መዳፋቸውን አነሱ ፤ “ ይቀጥሉ አቶ ኩራባቸው ” አሉ አቶ ማንደፍሮ ።

አቶ ኩራባቸው ፤ እድሜ ጠገብ አዛውንት ሲሆኑ እንደ ቀጭን ገመድ የሰለሉ ከሲታ ድመት ናቸው ።

“ እንደዚህ ያለ የምግብ እጥረት አይቼም ሰምቼም አላውቅም ፤ በእኔ ህይወት ዘመን ፤ በአባቶቼም ሆነ በቅድመ አያቶቼም ጭምር ። ምንም ነገር ብናደርድ ፤ የሚሆነው ሁሉ በጣም ግልጽ ሊሆን ይገባል ፤ እምነቴም በአንተ ላይ ጥያለሁ ጎልማሳው ማንደፍሮ ” አሉ።

ቀላ ያለችው ውብ ድመት በተራዋ መናገር ጀመረች ፤ “ ለምን ልጆቻችንን ወደ ሌላኛው መንደር ልከን ምግብ መኖር አለመኖሩን እንዲያጣሩ አናደርግም ? ”

“ እዚያም እንደዚሁ ድርቅ ቢኖርስ ? የሌላኛው መንደር ድመቶች ቢያጠቁንስ ? ወይም ውሾቹስ ቢሆኑ ? ” ሲል ወጣቱ ጥቁር ድመት በማሽሟጠጥ ተናገረ ።

አቶ ማንደፍሮ ከየአቅጣጫው የሚንሸራሸሩትን ሀሳቦች በጥሞና ይከታተላሉ ።

በስተመጨረሻም ከተቀመጡበት በኋለኞቹ ሁለት እግሮቻቸው ተነስተው ከቆሙ በኋላ ፤ የተሰብሳቢዎቹን ቀልብ ወደ እሳቸው እንዲሆን መዳፋቸውን አወዛወዙ ።

አመሰግናለሁ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ አሉ ። ነገር ግን የኔ ሀሳብ ትንሽ የተለየ ነው ። በሰርግ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው ።ትልቅ ድል ያለ ሰርግ።

እኛ የመርሃቤቴ ከተማ ድመቶች ፤ ወንዶች ልጆቻችን የአይጥ ሴት ልጆችን እንዲያገቡ መስማማት አለብን ።

ሁሉም ድመቶች በመገረም ማጉረምረም ጀመሩ። ጋብቻ ? በድመት እና አይጥ መካከል ? እርግጥ ነው ይህ የሚታሰብ አይደለም ።

አውቃለሁ ፤ አውቃለሁ ፤ አሉ አቶ ማንደፍሮ ፤ ያልተለመደም ነው ። ነገር ግን ሁላችንም ለጉዳዩ ሙሉ ልባችንን ከሰጠን በተግባር ማዋል ይቻላል ።

ወጣት ድመቶች ፤ የእናንትን ፈጣን እርምጃ እንፈልጋለን ።

አዛውንት ድመቶች ፤ የእናንትን ጥበብ እንፈልጋለን ።

ለአንዴ እና ለመጫረሻ ጊዜ እስከምናድናቸው ( ማደን / አደን ) እቅዳችን ከልብ እንደሆነ አስመስለን ማሳመን ይኖርብናል ።

ስብሰባው ሲጠናቀቅ አብዛኛዎቹ የድመት ቤተሰቦች ፤ መሪያቸው የጠነሰሱትን ሴራ በደስታ ተቀበሉ ።

ከአረጋውያን ድመቶችም ሶስቱ አንድ ጥቁር ፤ አንድ ነጭ እና አንድ ቀይ ድመቶች ሽማግሌ ሆነው ለአይጦች ቤተሰቦች እንዲላኩ ተመረጡ ።

በሚቀጥለው ቀንም የተመረጡት የድመት ሽማግሌዎች ለስጦታ የሚሆን የማሽላ እና በቆሎ ጥሬ ይዘው ወደ አይጦች ማህበረሰብ ሄዱ ።

አቶ ጠርጣራው የአይጦች ማህበረሰብ መሪ ናቸው ። ባህሪያቸው ልክ እንደ ስማቸውም ተጠራጣሪ ነው ፤ ስለሆነ ወዲያውኑ ነገሩን በጥርጣሬ መመልከት ጀመሩ ።

ነገር ግን ስሜታቸውን ሳያሳውቁ በአክብሮት ሲከታተሉ ቆዩ ።

ስለስጦታው እናመሰግናለን ‘ አሉ ለድመቶቹ ። በድርቁ ምክንያት እንደተጎዳችሁ ይገባናል ፤ በእርግጥስ ለመሆኑ ከእኛ መንደር ምን እግር ጣላችሁ ?

ሶስቱ ድመቶች ጥልቅ በሆነ ስሜት ውስጥ በመሆን ፤ የመጡበት አላማ ወንዶች ልጆቻቸውን ከአይጦች ሴት ልጆች ጋር እንዲጋቡ ለመጠየቅ እንደሆነ አስረዱ ።

እንደተለመደው ሁሉ አቶ ጠርጣራው ሀሳቡን በከፍተኛ ጥርጣሬ ተመለከቱት ።

ነገር ግን ድመቶቹ ሀሳባቸውን እስኪጨርሱ በትእግስት መጠባበቅ ጀመሩ። ማንኛውም ሁለት ቤተሰቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ ፤ በሀሳቡ ለመስማማት ጊዜ ወስደው ተወያዩ ፤ ከብዙ ውይይት እና ቅድመ ሁኔታውች በኋላ ሰርጉ እንዲደረግ እቅድ እንዲወጣ ተስማሙ ።

ሶስቱ ድመቶችም የደረሱበትን ለአቶ ማንደፍሮ አስታወቁ ። እሳቸውም ጭራቸውም በእርካታ ስሜት እያወዛወዙ የማህበረሰቡን አባላት እንደገና ሰበሰቡ።

በዚህ ታላቅ የሰርግ ቀን በርካታ አይጦች ይታደማሉ ሲሉ ለተሰበሰቡት ድመቶች ተናገሩ ።

ባህላችን በሚያዘን መሰረትም የሙሽራው ቤተሰቦች ፤ እኛ ማለት ነው ፤ ለሰርጉ ወደ ሙሽሪት ቤት እንጓዛለን።

ስለዚህ ሰርጉ ላይ የምትገኙ ደመቶች ሁሉ ፤ እናንተ ወጣቶች አና ቤተሰቦች ፤ እያንዳንዳችሁ ቢያንስ ቢያንስ ሁለት አይጦችን በመያዝ ለእራት ሰአት ይዛችሁ ወደ ቤት መመለስ አለባችሁ ።

እያንዳንዳችህ ሁለት ! ሰምታችኋል ?

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ ወጣት ልጃገረድ አይጦች የሰርጉን ወሬ ከሰሙ በኋላ ምንም ጊዜ ሳያጠፉ መልካመ መልካም የሆኑ ድመቶችን ለማግባት ዝግጅታቸውን ጀመሩ ። በሰርጋቸው እለትም እንዴት ውብ ሊሆኑ እንድሚችሉ በማሰብ በሀሴት ፈነጠዙ ።

ይህንን የሰሙት አንዳንድ ወጣት እና ጎረምሳ አይጦች ፤ልጃገረዶቻቸው ውብ ፍጥረት የሆኑ ድመቶችን ሊያገቡ በመሆናቸው በቅናት መንደድ ጀምውሩ ።

በዚህ መካከልም አቶ ጠርጣራው ፤ ልጆቻቸውን ለመዳር የተዘጋጁትን የአይጥ ወላጆችን በሙሉ ለስብሰባ ጠሩ ።

አንዳንዶቹም ጋብቻው የተቀደሰ ሃሳብ ነው ሲሉ አወደሱት ።

“ አስቡት እስቲ ” አሉ ሴት ልጆች ካሏቸው በርካታ አባቶች መካከል አንዱ ። ሁሉም ሴት ልጆቻችን የድመቶቹን ወንዶች ልጆች ካገቡ ፤ድመቶች ከዚህ በኋላ አይበሉንም ወይም አይገድሉንም ፡

በፍጹም አያደርጉትም ! ቤተሰብ ነው የምንሆነው ! ቤተሰባችንን ደግሞ አንበላም ! ’

ልክ ነው ፤ አንበላም አሉ አቶ ጠርጣራው። እውነተኛ ቢሆን ሀሳቡ በጣም የሚያስደስት ነው ። ነገ ግን ይህ እውነት ባይሆንስ?

እኛ ብልህ እንደሆንን ሁሉ ድመቶችም እንዲሁ እንደሆኑ እናውቃለን ። ስለሆነም ለመጠባበቂያ የሚሆን እቅድ ሊኖረን ይገባል ።

አቶ ጠርጣራው ያሰቡትም እቅድ ስለነበር ፤ ሀሳቡን ለማህበረሰቡ በጥንቃቄ አስረዱ ።

በምንኖርበት መንደር ምስጢራዊ የመደበቂያ ጉድጓዶችን የግድ መቆፈር ይኖርብናል ፤ ከዚያም የመደበቂያ ጉድጓዶችን ተከትሎ ወደ መሰባሰቢያ ቦታ የሚያዘልቁ በርካታ ጠባብ መንገዶችን እንቆፍራለን፡፡

እነዚህን መንገዶች በጣም በጥንቃቄ ማዘግጃት አለብን ፤ መግቢያቸውን በጣም ጠባብ በማድረግ ድመቶች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ማደረግ አለብን ።

አይጦቹም በተነገራቸው መሰራት ለመስራት ተስማሙ። ልብ በሉ ፤ እንደ ተጠራጠርናቸው በፍጹም መንገር የለብንም ። እያንዳንዳችን በጥቅንቃቄ ነገሩን መከታተል ይኖርብናል ።

ታላቁ ቀን እየተቃረበ ስለመጣ ሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ የሆነውን ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ ።

በስተመጫረሻም ፤ ቅዳሜ ከሰአት ፤ ወጣት መልከ መልካም ወንድ ድመቶች በታላቅ ደስታ እና ፈንጠዝያ ተሞልተው ፤ ከጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ሴት ሙሽሮች ቤት አቀኑ ።

የአይጥ ሙሽሮች እና ቤተሰቦቻቸም ሊቀበሏቸው በመራቤቴ አካባቢ የሚዘወወተረውን ፤ ጭብጨባ በባህላዊ የሰርግ ዘፍን እና ጭፈራ እያቀለጡ ወጡ ።

አናስገባም ሰርገኛ እደጅ ይተኛ

አናስገባም በሩን ሰርገኛውን

በምላሹም ድመቶቹ በሁሉም ዘንድ በጣመ የተለመደውን የሰርግ ዘፈን እንዲህ እያሉ መዝፈን ጀመሩ ፦

ሃይ ሎጋ ሀይ ሎጋዮ ሆ

ሃይ ሎጋ ሀይ ሎጋ ሆ

ሁሉም በደስታ ተውጠው እየዘፈኑ እና እየጨፈሩ ሳለ ፤ የድመት ቤተሰቦች ሌላ ዘፍን መዝፈን ጀመሩ ፤

ዘፈኑም ማንም ሰው ሰምቶት የማያውቅ እና በምንም አይነት የባህላዊ የሰርግ ዘፈን አካል ያልሆነ ነው።

ሚያው ሚያው ዳር ዳሩን ክበበው

ሚያው ሚያው ዳር ዳሩን ክበበው

ከዚያም በንግግራቸው መሰረትም ድመቶቹ ስፋ ሰፋ በማድረግ አይጦቹን በመክበብ መሀል ውስጥ ማስገባት ጀመሩ ፤

ነገር ግን አቶ ጠርጣራው እንዳዘዙት ፤ አይጦቹ የድመቶቹን እንቅስቃሴ በጥርጣሬ እየተከታተሉ ነበር። ከዚያም እነሱም ለእለቱ ያዘጋጁትን የሚስጥር ዘፈን ለወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ምልክት ለመስጠት መዝፈን ጀመሩ ፤

እኛም አውቀናል

ጉድጓድ ምሰናል

እያሉ እየዘፈኑ ከድመቶቹ በበለጠ ፍጥነት በሩጫ ፍጥነት ተበታትኑ።

ድመቶቹም ይህንን በፍጽም አልጠበቁም ነበር ፤ በመጀመሪያ አንድ ድመት ፤ ከዚያ ተጨማሪ ድመቶች ተስፋ በቆረጠ መንፈስ የሞት ሽረታቸውን አይጦቹን ከከበቡበት ወጥተው አንድ በአንድ ማባረርና ማሯሯጥ ጀመሩ ፤

ነገር ግን ብልህ እና በደንብ የተዘጋጁት አይጦች እየዘለሉ ወደ ጉድጓዶቻቸው ገቡ ።

ድመቶቹ ተከታትለው ሊያዟቸው ቢሞከሩም ሙከራቸው በተደጋጋሚ ያለውጤት መና ቀረ፤ ድመቶቹም አይጦቹ እንዳሞኟቸው እንዲሁም በብልጠት እንደበለጧቸው ሲረዱ በንዴት መንፈስ ጉድጓዱን መቧጨር ቢጀምሩም በጥንቃቄ የተስሩ ጉድጓዶችን ማለፍ አልቻሉም ።

በአንጻሩም ከመሬቱ ስር አምልጠው የገቡት አይጦች እንደተሳባሰቡም በአስቸኳይ ቆጠራን አደርጉ ፤

የጠፋ አለ ?

እናቱን አባቱን ያጣ አለ ?

ቤተሰቦቻቸውን እና ዘመዶቻቸውን ያጡ አሉ ?

ምንም አልነበረም ። ድመቶቹም አንድም አይጥ አልያዙም ነበር ፤

ድመቶች አንገታቸውን ደፍተው ፤አላማቸውን ባለማሳካታችው በአፍረት ተውጠው ወደ ማህበረሰባቸው ተመለሱ ።

የውርደት ሰሜቱም ከአይጦች ብልሀት ጋር ውድድር በያዘው መሪያቸው ላይ በግልጽ ይታይ ነበር፤

እናም ሁለተኛ ሆነው ቀሩ ።

ታሪኩ በዚህ ሁኔታ ተጠናቋል ፤ በባህላችን መሰረት ተረት አውርተን ስንጨርስ እንዲህ በማለት እንሰናበታለን።

ተረቴን መልሱ

 አፌን በዳቦ አብሱ

መታሰቢያነቱ ተረትን በመተረት ታላቅ ተሰጣኦ ላላት ለአያቴ ይሁንልኝ ።

ይህ ተረት በቃል ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ ሲሆን ፤ በልጅነታችን የነገረችን አያታችን ወ/ሮ ትርንጎ ዝሜ ናት። አያታችን ተረትን የምትነግረንም እኛን ስነ ስርአት ለማስተማር ፤ ለማዝናናት እና አንዳንዴም ለተግሳጽ ነበር።


Share